Maleda
ማለዳ ማለዳ ፍቅርሽ ለኔ ነው እንግዳ (2×)ያን አይታ የልብ ውበት ደስ የሚል የሰው ፅጌ ታምራለች ያኔ ያለችው አንቺን ነው ለካ እቴጌ አይደለም በቁንጅናሽ መልክሽ ላይ በተሳለው ያስባለሽ የሴት አሪፍ ሆነሽ መገኘትሽ ነውማለዳ ማለዳ ፍቅርሽ ለኔ ነው እንግዳ (2×)እያየኝ ሰው ሁሉ ለፍቅር ማነሴን ይሄው ብዬ ብዬ ሰጠውሽ ራሴን አታውቂም ካሳቤ ወተሽ እንኩአን ለአንዴ ሌላ ነገር ማሰብ ሊሳነኝ ነው እንዴ እቱ…….. እቱ ወይ ፍቅር ጉልበቱ እቱ…… እቱ ሆኗል ፍቅርሽ ብርቱ በፀሃይም አብሬሽ በጨረቃም አብሬሽ አወጣው ሌላ አመል ካቅም በላይ አፍቅሬሽ አይንሽን ወርውረሸው አሳርፈሽ ካይኔ ላይ ወድያ ወዲ እንዳልል አረግሺኝ ሌላ እንዳላይ ማለዳ ማለዳ ፍቅርሽ ለኔ ነው እንግዳ (2×) አውዳመቱ ፍቅርሽ ስብስ ከዋዜማ ልብ ያስጎዘጉዛል እንኩአንስ ቄጤማ እየመጣሽ ደጄ በፍቅር መንገድ ሁሌም ስራዬ ነው ማለት ሽርጉድ እቱ…….. እቱ ወይ ፍቅር ጉልበቱ እቱ…… እቱ ሆኗል ፍቅርሽ ብርቱ