TAGESEGN
እስቲ ትንሽ ታገሰኝ እወቀኝ ልወቅህ
እንዴት በአንድ ጀምበር ያልከውን ልመን
እስቲ ትንሽ ታገሰኝ እወቀኝ ልወቅህ
እንዴት በአንድ ጀምበር ያልከውን ልመን
ያሰብኩት ጠፋኝ ጨዋታው ቀልቤን ነጠቀኝ
ልቤ ታወከ ሁኔታ እጅግ አስፈራኝ
በእርግጥ አመንኩት እንደሱም ሲሆን እፈራለው
ነገር ሲዋከብ ከስሩ መመርመር እሻለው
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ
እስቲ ትንሽ ታገሰኝ እወቀኝ ልወቅህ
እንዴት በአንድ ጀምበር ያልከውን ልመን
እስቲ ትንሽ ታገሰኝ እወቀኝ ልወቅህ
እንዴት በአንድ ጀምበር ያልከውን ልመን
ነፍስ የሚያማልል አስደሳች ቢመስልም ማየው
መብሰል አልሻም በቅጡ መርምሬ ሳላየው
ከሀሳብ ሲቀድም ተግባር ሆን ብለው ካላዩት
በዚህ ግርግር የጠፋም እንኳን ላያገኙት?
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ